የደቡብ ክልል አደረጃጀት ጥናት የምክክር መድረክ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

የደቡብ ክልል አደረጃጀት ጥናት የምክክር መድረክ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) በአዲስ አበባ እና በአዳማ ሲያካህድ የቆየውን የክልል አደረጃጀት ጥናት ምክክር መድረክ ማጠቃለያ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል።

በውይይት መድረኩ ላይ በፌደራል ደረጃ የሚገኙ አመራሮች እና የቀድሞ ነባር አባላት ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ሲያካሄዱት የነበረው ውይይት እንዲሁም የአዳማው የአዲስ አበባ ከተማ የደኢህዴን አመራር መድረክ ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በዚሁም በውይይቱ ላይ የተንሸራሸሩ ሀሳቦች በየቡድን መሪዎች በሪፖርት መልክ ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡

መድረኩን እየመሩ የሚገኙ የደኢህዴን ሊቀ መንበርና የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል፣ ውይይቶቹ አመራሮቹን በአንድነት ውስጥ ያለውን ሀይል እንዲገነዘቡ ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡

በዛሬው ውይይት ላይ በደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥናትና በመጨረሻው ምክረ-ሃሳብ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶች መኖራቸውንና ሌሎች የተለያዩ ወቅታዊ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡

ሰሞኑ ከክልል ውጭ ባሉ የደኢህዴን አመራሮች ደረጃ የደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥናት ዙሪያ ውይይት ሲካሄድ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡