ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሳዑዲ  አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሳዑዲ አረቢያ አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በዚህን ወቅት የሳዑዲው አልጋወራሽ ኢትዮጵያ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት እንዲፈፅሙ  የነበራትን የሸምጋይነት ሚና አድንቀዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት ሳዑዲ  እንደምትደግፍ መናገራቸውን የዘገበው የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ነው።

የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል ስልጣን መጋራት የሚያስችላቸውን የመጨረሻ ስምምነት ከቀናት በፊት መፈራረማቸው ይታወሳል።