ኢትዮጵያና አሜሪካ የሕግ ማስከበር እና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት ተፈራረሙ

የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚልና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይኖር መንግሥቶቻቸውን ወክለው የሕግ ማስከበር እና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱም ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና ለፌደራል ፖሊስ እንዲሁም ለፍትህና ሕግ ማስከበር አካላት ድጋፍ በመስጠት የሕግ ማስፈጸም እና የፍትሕ ዘርፉን ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።