ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአየርላንድ አምባሳደር ሚስ ሶንጃ ሃይላንድን አሰናበቱ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የአየርላንድ አምባሳደር ሚስ ሶንጃ ሃይላንድን አሰናበቱ፡፡

አምባሳደሯ ባለፉት ሁለት ዓመታት ቆይታቸው በኢትዮጵያና በአየርላንድ መካከል የነበረው ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ላደረጉት አሳተዋፅኦ ፕሬዝዳንቷ አመስግነዋል፡፡ በቀጣይ ለሚኖረው ግንኙነትም በተግባር ካዩት እውነታ ተነስተው በኢትዮጵያ ያለውን የሀገር ግንባታ እንቅስቃሴ እንዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡

ተሰናባቿ የአይርላንድ አምባሳደር ሚስ ሶንጃ ሃይላንድ በበኩላቸው፣ በቆይታቸው በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለተደረገላቸው ሁለንተናዊ ድጋፍ አመስግነው በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንቨስትመንትና ሌሎች ዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ መረጃው የፕሬዝዳንት ጽጽቤት ነው፡፡