የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ እየተካሄደ ነው

የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ መድረክ በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ነው፡፡

ጨፌ ኦሮሚያ በ4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤው የዜግነት አገልግሎት አዋጁን በማጽደቅ የክልሉ መንግስት ስራ ላይ ያዋለው መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ አርቲስቶችና ሌሎች ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡