ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የለውጥ ዙሪያ የሚወያይ ኮንፈረንስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ አስጀመሩ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት፣ ወቅታዊ ሁኔታ፣ መፃኢ እድል እና ስጋቶች ዙሪያ የሚወያይ ኮንፈረንስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ አስጀመሩ፡፡

ፕሬዝዳንቷ ኢትዮጵያ በታሪኳ ወሳኝ የሚባል የለውጥ መንደርደሪያ ላይ እንደምትገኝ ገልፀዋል፡፡

ይህ ወቅት ኢትዮጵያ የህዝቦቿን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስና ፍላጎታቸውን ለማርካት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ ጅማሮ ላይ እንደምትገኝም አብራርተዋል፡፡

በዚህ ሂደት ላይ የህዝቡን አንድነትና ተነሳሽነት ለማጠናከር ከቃላት ባለፈ በተግባር የሚገለፁ በርካታ መሰራት ያለባቸው ተግባራት ከፊት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ድረስ የታዩት ተስፋዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ለሚፈለገው ድል ለመድረስ ከህዝቡ አቅም በላይ እንደማይሆን አምናለሁ ያሉት ፕሬዝዳንቷ ለዚህ ሂደት አቅጣጫ የሚያመላክት ፍሬያማ ውይይት ከኮንፈረንሱ እንደሚጠብቁ አብራርተዋል፡፡ መረጃው የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ነው፡፡