አዲሱ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ ፀደቀ

ተሻሽሎ የቀረበውን የኢትዮጰያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ረቂቅ አዋጅን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፀደቀው፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ክርክር ካደረገ በኋላ ነው በሙሉ ድምፅ ያፀደቀው፡፡

ይሁን እንጂ ወንድ እና ሴት ተወዳዳሪዎች እኩል ድምጽ ቢያገኙ ሴት ተወዳዳሪዋ እንደምታሸንፍ በረቂቅ አዋጁ ላይ ቢቀመጥም ም/ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጎታል።ምክንያቱ ደግሞ የፆታ እኩልነትን መርህ የሚፃረር የሚል ነው፡፡

ዛሬ በፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የመንግስት ሰራተኛ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሆኖ በምርጫ ቅስቀሳና በውድድር ቢሳተፍ ያለ ደመወዝ ፈቃድ ማግኘት እንደሚችል ይደነግጋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች አባሎቻቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ከአባልነት ለመሰረዝ ቢፈልጉም ያለ ፍርድ ቤት ፈቃድ ማሰናበት እንዲችሉም ፈቃድ የሚሰጥ ተብሏል፡፡

በፀደቀው ረቂቅ አዋጅ መሰረት ለግል ለተወዳዳሪዎች መንግስት ድጋፍ እንደሚሰጥም ተደንግጓል፡፡

ምንጭ ፡ ኢቢሲ