ጠ/ር ዐብይ አህመድ በ7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጃፓን ዮኮሀማ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በ7ኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት /TICAD/ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጃፓን ዮኮሀማ ገቡ። 

ሰባተኛው የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት መድረክ ዘንድሮ ለ7ኛ ጊዜ በመካሄድ ላይ ሲሆን፤ 
ቀደም ብሎ በሚኒስትሮች ደረጃ የጀመረው መድረኩ ቀጥሎ በመሪዎች ደረጃ ይካሄዳል።

በጃፓን ዮኮሃማ በሚካሄደው በዚሁ ጉባኤ የአፍሪካና የጃፓን መሪዎች እንዲሁም የጃፓን ባለሃብቶችና የንግድ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የቶኪዮ ለአፍሪካ ልማት ጉባኤ በ1993 እ.ኤ.አ አፍሪካን ከጃፓን ጋር በልማት ለማስተሳሰር የተጀመረ ነው።

በዘንድሮው ጉባኤ መድረክ ቴክኖሎጂን እና ኢኖቬሽንን በማጣመር ለአፍሪካ ልማት በሚውልበት ሁኔታ ላይ እና በአፍሪካና በጃፓን የንግድ ትስስር ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።