ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በናዚ የተጨፈጨፉ አይሁዳውያን ማስታወሻ ማዕከልን ጎበኙ

በእስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በናዚ የተጨፈጨፉ አይሁዳውያን ማስታወሻ ማዕከልን ያድ ቫሼምን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለዑካቸው በማእከሉ የሚገኙትን የመታሰቢያ ሙዚየም፣ የህፃናት መታሰቢያን እና አዳራሽ ጎብኝተዋል

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማእከሉ የክብር መፅሃፍ ላይ መልእክታቸውን አስፍረዋል።