የጋራ ምክር ቤቱ በቅርቡ የጸደቀው የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ አዋጅ በአስቸኳይ ተመልሶ እንዲታይ ጠየቀ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የምርጫ አዋጅ በአስቸኳይ ተመልሶ እንዲታይ ጠይቋል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ በቅርቡ የፀደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ አሁን ባለበት ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ በቀጣዩ ምርጫ የማይሳተፍ መሆኑን አስታውቋል።

ይህ አቋምም ከ107 ፓርቲዎች ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑትን ፓርቲዎች የጋራ አቋም የሚያካተት መሆኑ ተነግሯል ፡፡

መንግስት አዋጁን በዚህ መልኩ ተግባራዊ ካደረገ የሚካሄደው ምርጫ ተዓማኒነት የሌለውና ሀገሪቷንም ወደ ችግር የሚዳርግ ይሆናል ብሏል ምክር ቤቱ ፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ  የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት መልሶ እንዲታይ የጠየቀ ሲሆን፤ ጊዜው ካጠረም የምርጫ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቋል፡፡

ጥያቄያቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጀምሮ እስከ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋማትና ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው ምላሽ እንዲሰጡም ነው የጠየቁት፡፡