የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት ለጉብኝት ክፍት ሆነ

የቀድሞው ማዕከላዊ እሥር ቤት ዛሬ ለጉብኝት ክፍት ሆኗል፡፡

ከዛሬ ጳጉሜ 1 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. እሥር ቤቱ ለሕዝብ እይታ ክፍት እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡

መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፀምበት እንደነበረ በማመን እንዲዘጋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ እና ሌሎች የፍትህ ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የቀድሞው እስር ቤት ለሕዝብ እይታ የበቃው።