የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሞስኮ ገቡ

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ሞስኮ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ለቭሮቭ ጋር ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

በዚሁ ጉብኝት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ከሩሲያ ወገን ጋር በሚደረግ ዉይይት እንደሚሣተፉም ይጠበቃል።

ጉብኝቱ የሁለቱን አገሮች የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የልማት ትብብር እንዲሁም የሣይንስና ቴክኖሎጂ ትብብር እንደሚያሳድግ እምነት ተጥሎበታል፡፡

ሚኒስትሮቹ ሞስኮ ሲደርሱ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ አምባሳደር ጆርጂ ቶድዋ፣ በሩሲያ የኢፌዲሪ አምባሳደር አቶ ዓለማየሁ ተገኑ እንዲሁም የኤምባሲው ባልደረቦች አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በፈረንጆቹ 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።