የኢፌዴሪ አየር ሃይል ለ735 አባላቱ የማእረግ እድገት ሰጠ

የኢፌዴሪ አየር ሃይል ለ735 አባላቱ የማእረግ እድገት የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 10ሩ ከመስመር መኮንንነት ወደ ከፍተኛ መኮንንነት የማእረግ እድገት ያገኙ ናቸው፡፡

በተቋሙ ውስጥ ለረጅም አመታት ላገለገሉ እንዲሁም ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን አገልግለው ጡረታ ለወጡ 56 የቀድሞ አባላቶቹም የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል።

በአየር ሃይል ደረጃ በተለያዩ ስራዎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላስመዘገቡ የተለያዩ የስራ ክፍሎችም ማበረታቻ ሰርተፍኬት መሰጠቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም የኢፌዴሪ አየር ሃይል ከመላው ሰራተኞች የሰበሰበውን 200 ሺህ ብር ለኢትዮጵያ ልብ ህሙማን መርጃ ማእከል መለገሱን ኢቢሲ ዘግቧል።