በቡራዩ ከተማ በፖሊስ ካምፕ ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ትናንት ምሽት 1:30 ገደማ በቡራዩ ከተማ በኦሮሚያ ፖሊስ ማረፊያ ቦታ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት 9 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

ጥቃት ከደረሰባቸው 9 ሰዎች መካከል አንዱ ሕክምና ተደርጎለት ወደ ቤት የተመለሰ ሲሆን፣ ስምንቱ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ሆስፒታል ተልከው ሕክምና እያገኙ ነው ተብሏል፡፡

ጥቃት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ አንዷ ለፖሊሶች ምግብ የምታዘጋጅ እንደሆነች ተገልጿል፡፡

በቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ የሸኔ ሽፍታ አባላትና ሌሎች ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር
ውለዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን ከሚገልጹ መረጃዎች ጋር እንደተያዙ ነው ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡