3ኛው የሰላም ጉዞ በድሬዳዋ ከተማ ይደረጋል

ሶስተኛው የሰላም ጉዞ በድሬዳዋ ከተማ እንደሚደረግ ተገለጸ፡፡ 

ስለ ሰላም፣ መቻቻል፣ ፍቅር እና አንድነት የሚሰብክ የሰላም ጉዞ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ድሬዳወ የሚደረግ ሲሆን፤ በጉዞው አንጋፋ የኪነጥበብ ሰዎች የሚሳተፉበት ይሆናል ተብሏል።

መስከረም 17 ቀን 2012 ዓ.ም በሚካሄደው የሰላም ጉዞ መርሃግብር የእግር ጉዞ፣ የደም ልገሳ፣ ችግኝ የመንከባከብ እና የኪነጥበባት ስራዎች የሚቀርቡ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም የሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና የኃይማኖት አባቶች የሚሳተፉበት ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የሚካሄደው የሰላም ጉዞው የህብረተሰቡን ፍቅር እና ሰላም እንዲሁም አብሮነቱን ለማጠናከር የሚደረግ መርሃግብር እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ደም በመለገስ ወገኖችን ከሞት ለመታደግና አንድነትን ለማጠናከር፣ ችግኞችን በመትከል በተፈጥሮ ፀጋ ለሌሎች መትረፍ እና ሌሎች የህብረተሰቡን አብሮነት ሊያጠናክሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ስለሰላም የሚሰበክበት መድረክ ስለመሆኑ ጉዞዉን የሚመሩ አርቲስቶች ተናግረዋል፡፡  

አርቲስቶቹ ሁሉም የህብረሰተብ ክፍል ለሰላም እና ለአንድነትን በመረዳዳትና በመነጋገር መስራት እንዳለበት ተናግረዋል፡

ይህ የሰላም ጉዞ ከዚህ ቀደም በቡታጅራ እና ሚዛን ቴፒ ከተሞች ተካሂዶ ውጤታማ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡ በቀጣይም አስራ አራት የሀገር ውስጥ እና አስር ከሀገር ውጭ ተመሳሳይ ጉዞዎች ይደረጋሉም ተብሏል፡፡