2ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት/ኢጋድ/ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ስብሰባውም በዋናነት በቀጠናው አገራት ያለውን የስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ በተደረሰው የናይሮቢ ስምምነት አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ስምምነቱ የቀጠናው አገራት ስደተኞችን መንከባከብ፣ ስደተኞች ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በማስቀረትና ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡

ስደተኞች የሚሄዱባቸው አገሮችን ጫና ለመቀነስም የሚሰሩ የጋራ ስራዎች መኖራቸው ተነግሯል፡፡

የሚኒስትሮቹ ስብሰባ ሰደተኞች ወደ ነበሩበት ከመመለስ ጀምሮ በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ እንደሆነም ተመልክቷል፡፡

በኢትዮጵያ ከተለያዩ የጎረቤት አገራት የተወጣጡ 1 ሚሊዮን ስደተኞች እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡