ግብፅ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ ያቀረበችዉን ሃሳብ ኢትዮጵያ ዉድቅ አደረገች

የዉኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ግብፅ በግድቡ ዙሪያ ከበፊቱ የሶስትዮሽ ስምምነት ያፈነገጠ ሀሳብ ማቅረቧንና ሀሳቡ በኢትዮጵያ በኩል ዉድቅ መደረጉን አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰሞኑን በጉዳዩ ዙሪያ በካይሮ በተገረገዉ ውይይት ምክክር ሀሳቡን እንዳልተቀበለችዉ ያስታወሱት ሚንስትሩ ሌላ ድርድር እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ በጉዳዩ ዙሪያ  ከመስከረም 19-22፣ 2012 ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ስምምነት ያልተፈጠረባቸው ግብጽ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተሞላ በኋላ በየዓመቱ ከ45ሚሊየን ሜትር ኩብ ውሃ ሊደርሰኝ ይገባል፤ እና የአስዋን ግድብ ከ167 ሜትር ከፍታ በታች እንዳይወር ኢትዮጵያ ሃላፊነቱን ልትወስ ይገባል በሚል በማቅረቧ ነው ተብሏል።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ግብፅ ይህንና በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ ያቀረበችዉን ሃሳብ ኢትዮጵያ ዉድቅ ማድረጓን ዶ/ር ኢነርጂ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ አስታውቃል።

ሚንስትሩ እንዳሉት ጉዳዩን ከሶስቱ ሀገሮች የተዉጣጣ ገለልተኛ የሳይንስና ምርምር ብሔራዊ ኮሚቴ ያጠናዋል ፡፡