የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳ ከጥቅምት 18 እስከ 22 ድረስ እንደሚካሄድ ቦርዱ ገለፀ

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳ ከጥቅምት 18 እስከ 22 ድረስ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ::

የሲዳማ ክልልነት ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሃ-ግብር መሰረት የቅስቀሳ ጊዜ ከመስከረም 23- 28 ቀን 2012 ዓ.ም በሚል ታቅዶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡

ነገር ግን የህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳው የመራጮች ምዝገባ ከሚደረግበት ጊዜ ጋር የተቀራረበ ቢሆን ይሻላል በሚል ስለታመነበት የቅስቀሳ መርሃ ግብሩ ከጥቅምት 18- 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት እንዲሆን ተብሎ ተሻሽሏል፡፡

ቦርዱ በአፈጻጸም ጉዳዮች የተነሳ የሚኖሩ የቀናት ለውጥና መሸጋሸጎችን ለወደፊትም ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡