ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ጋር ባደረጉት ቆይታ ተጨማሪ የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች እንዲኖሩ ለማድረግ ጥናት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ይህ ተግባራዊ መሆን ያለበት ጥናትና እውቀትን መሰረት አድርጎ መሆን እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አፋን ኦሮሞን ጨምሮ ሌሎች ቋንቋዎችን የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡