የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ አመት የሥራ ዘመን ዛሬ በይፋ ይከፈታል

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ አመት የሥራ ዘመን ዛሬ በይፋ ይከፈታል፡፡

በመክፈቻው ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተገኝተው ለሁለቱም ምክር ቤቶች የመክፈቻ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የሀይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች በሂደቱ ላይ እንደሚገኙ ይጠበቃል።

ዋልታ ቴሌቪዥንም የምክር ቤቱን ውሎ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በቀጥታ እንደሚያስተላልፍ ከወዲሁ ይገልጻል፡፡