ለሶስት ክልሎችና አንድ የከተማ አስተዳደር የምርጫ ክልል ኃላፊነት በቂ አመልካቾች አለመቅረባቸው ተገለጸ

ለሐረሪ ክልል፣ ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ ለጋምቤላ ክልል እና ለአማራ ክልል የምርጫ ክልል ኃላፊነት በቂ አመልካቾች አለመቅረባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል፡፡

ቦርዱ ለዘጠኙ ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ክልል ኃላፊነት ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመመደብ የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

መስፈርት የሚያሟሉ እና በሶስቱ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር መስራት ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የማመልከቻ ጊዜው መራዘሙን ቦርዱ ገልጿል፡፡

የማመልከቻ ጊዜው በአንድ ሳምንት በመራዘሙ አመልካቾች ከዛሬ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ማመልከቻቸውን ማስገባት እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡