የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ አምዶክ አዲስ አበባ ገቡ

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ አምዶክ ዛሬ ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲፈደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ከሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ እንዲሁም የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

(ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)