በአንድነት ፓርክ ምረቃ ላይ የተጋበዙ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

አዲሱ የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪርና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አብደላሂ በአንድነት ፓርክ ምረቃ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

መሪዎቹ ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ የገቡት በታላቁ ቤተ መንግስት በተገነባው የአንድነት ፓርክ ይፋዊ የምርቃ ስነ ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት ለመገኘት ነው፡፡

መሪዎቹ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ከፍተኛ የመንግስት ባስልጣናትና የየሀገራቱ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላት ተቀብለዋቸዋል፡፡

በአንድነት ፓርክ ይፋዊ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ መሪዎችም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡