ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከፊንላንድ ፕሬዝደንት ሶሊ ኒኒስቶ ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፊንላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ሶሊ ኒኒስቶን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የፊንላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሶሊ ኒኒስቶ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ኦፊሴላዊ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ማታ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተጨማሪ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮች ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዝዳንት ሶሊ ኒኒስቶ በአየር ንብረት ለውጥ እና የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረታቸውን ባደረጉ ሁለት ትላልቅ ኮንፈረንሶች ላይም ንግግር ያደርጋሉ።

እንዲሁም በፊንላንድ ድጋፍ የሚደረግለትን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደሚጎበኙም ይጠበቃል።

ምንጭ፡-ኢቢሲ