ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፋር እና ከሶማሌ ክልል አመራሮች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፋር እና ከሶማሌ ክልል አመራሮች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፋርና የሶማሌ ክልላዊ ብሔራዊ መንግሥት አመራሮችን አግኝተው በክልሎቹ የጸጥታ ሁኔታን ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በአፋር እና ሶማሌ ክልል ከሰሞኑ የሰላምና ጸጥታ መረጋጋት እንዲፈጠር የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች መካሄዳቸው ይታወሳል።