የኮምቦልቻ -ባቲ -ሚሌ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ከ82 በመቶ በላይ ተጠናቀቀ

የ133 ኪሎሜትር እርዝመት ያለው የኮምቦልቻ-ባቲ-ሚሌ የአስፋልት መንገድ የግንባታ ሥራ ከ82 በላይ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ ።   

የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለዋልታ እንደገለጹት በጠጠር ደረጃ የነበረው የኮምቦልቻ-ባቲ-ሚሌ በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ግንባታው  እየተካሄደ  ይገኛል ብለዋል ።

የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ  በአማራና በአፋር ክልል መካከል ያለውን የትራፊክ ፍሰትና የአካባቢውን ህብረተሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳድግ  መሆኑን  አቶ  ሳምሶን አክለው ገልጸዋል ።

የመንገድ ፕሮጀክቱ በሁለት ኮንትራት ተከፋፍሎ ግንባታው እየተከናወነ ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ  የሆነው የኮምቦልቻ-ቡርቃ የ60 ኪሎሜትር መንገድ ዦንግሜይ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የተባለ የቻይና ዓለም ዓቀፍ  የሥራ  ተቋራጭ ድርጅት ግንባታው እየተካሄደ እንደሚገኝ አቶ ሳምሶን አመልክተዋል ።

እንደ አቶ  ሳምሶን  ገለጻ የፕሮጀክቱ የሁለተኛው ኮንትራት ግንባታ 73 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን ሻንግሃይዌይ ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ግሩፕ የተባለው የቻይና ዓለም አቀፍ የሥራ  ተቋራጭ  ድርጅት እየተገነባ ይገኛል ።

የኮምቦልቻ-ባቲ-ሚሌ የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ከዓለም ባንክ በተገኘ  ብድርና ከኢትዮጵያ  መንግሥት በተመደበ   በአጠቃላይ በ2ነጥብ 8 ቢሊዮን  ብር ወጪ ግንባታው እየተከናወነ መሆኑን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ።         

የ133 ኪሎሜትር እርዝመት ያለው የኮምቦልቻ-ባቲ ሚሊ የአስፋልት መንገድ የግንባታ ሥራ ከ82 በላይ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ ።   