የአዲስ  አመት  በዓል  በሰላም  እየተከበረ  ዋለ   

የ2009  ዓም  የአዲስ  ዘመን  መለወጫ  በዓል በሰላም፣ በደስታና በድምቀት እየተከበረ መዋሉን  የተለያዩ   የአዲስ አበባ  ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ ።   
ዋኢማ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው የተለያዩ የአዲስ አበበ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት የ2009 የአዲስ  ዘመንን  በሰላም ፣ በደስታና በፍቅር  ማክበራቸውን ።
አዲሱ ዘመን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ፣ የሰላም፣ የፍቅርና የመከባባር   እንዲሆንለት መልካም  ምኞታቸውን ገልጸዋል ።  
በከተማዋ  የካራ ቆሬ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ወይሳ ጥርአይሎ እንደገለጹት ከዋዜማው አንስቶ  የአዲስ ዘመን  መለወጫ በዓሉን ለማክበር ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውንና በሰላም ማክበራቸውን ገልጸው አዲሱ ዓመት  ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ የሰላም ፣ የደስታና የዕድገት እንዲሆን ተመኝተዋል።  
ወጣት ዳናዊት  ለምለም በበኩሏ  አዲሱን ዓመት ካለፉት ዓመታት በህይወቷ ላይ የተሻለ ለውጥ  በማምጣት የምትጥርበት መሆኑን ጠቁሟ   ወጣቶች  እራሳቸውን  በመለወጥ  ለአገር ዕድገት  አስተዋጽኦ የሚያበረክቱበት ዘመን እንዲሆን ተመኝታለች ።
በአዲስ አበባ ከተማ የኮልፌ ቀራንዮ አካባቢ  ነዋሪ  የሆነው ከበደ እሸቱ የዘንድሮ የአዲስ ዓመት በዓል በአዲስ መንፈስ  እንደተቀበለው በመግለጽ ሁሉም  ዜጋ  በአዲሱ ዓመት ለሰላም ፣ ለዴሞክራሲና ለልማት  የሚቆምበት  እንዲሆን ተመኝቷል ።
ሌላዋ  የአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ  የሆነቺው  ዓለም  ተሰማ   አዲሱን  ዓመት  የምትቀበለው   ከባለፉት ዓመታት  በተሻለ  መልኩ ኑሮዋን  የማሻሻል  የያዘችውን ዕቅድ ለማሳካት ከልብ በመነሳት ነው ብላለች ።