የገዳ ስርዓት ለዘመናዊው የዴሞክራሲ ስርዓት መሰረት ነው

የገዳ ስርዓት ለዘመናዊው የዴሞክራሲ ስርዓት መሰረት የሆኑ እሴቶች ያሉት መሆኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ የመመዝገብ አቅም ፈጥሮለታል ተባለ።

ስርዓቱን በዩኔስኮ የማስመዝገብ ሂደቱ በመጪው ህዳር ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።

የገዳ ስርዓት የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ሲተገብረው የቆየ፣ እያዳበረውም የመጣ የማንነቱ መገለጫ ታሪኩን ፣ እምነቱንና አገር በቀል እውቀቶችን አካቶ የያዘ ጥንታዊ ዴሞክራሲያዊ የአስተዳደር ስርዓት እንደሆነ ይነገራል።

ስርዓቱ በኦሮሞ ሕዝብ የትውልድ ቅደም ተከተል ላይ በመመስረት በአምስት የተለያዩ መደቦች የሚደራጅና በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ኅብረተሰቡን ለመምራት በየስምንት ዓመቱ ሠላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚከናወንበትም ነው።

የሞጋሳ ፣ የጉዲፈቻ፣ የጉማ፣ ዋቄፈና፣ የሲንቄና ኢሬቻ ስርዓቶች በገዳ ስርዓት መገለጫዎች ከሚካተቱ እሴቶች መካከል ናቸው።

በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የገዳን ስርዓት ለማስመዝገብ የተቋቋመ የጥናት ቡድን አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ ግርማ ለኢዜአ እንደገለጹት ስርዓቱ ለተቋሙ በ2007 ዓ.ም የማስመረጫ ሰነድ ከተላከበት ጊዜ ጀምሮ ሲገመገም ቆይቷል።

በሰነዱ የገዳ ስርዓት የዘመናዊ ዴሞክራሲ እሴቶችን የሚያንጸባርቅና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የአስተዳደር ስርዓት መሆኑን ማሳየትም ተችሏል።

በበይነ መንግስታት ሲገመገም የቆየው የማስመረጫ ሰነዱ ረቂቅ ውሳኔም በመጪው ጥቅምት የሚሰጥ ሲሆን ይህም የጎደሉ ነገሮችን አስተካክሎ ለዋናው ውሳኔ ለማቅረብ ያግዛል ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው የበይነ መንግስታት ኮሚቴው በሚቀጥለው ህዳር ወር 11ኛውን የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥበቃ ጉባዔ በአዲስ አበባ ሲያካሂድ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የማስመረጫ ሰነዱ ደረጃውን ጠብቆ መዘጋጀቱና መቅረቡ፣ ቅርሱ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶችን የማይጻረር መሆኑ፣ ለዘላቂ ልማት ያለው አስተዋጽኦ፣ ኢትዮጵያ የኮሚቴው አባልና የጉባዔው መሪ አገር መሆኗ ለስኬቱ አስተዋጽኦ ያደርጋል” ብለዋል።

የቅርሱ መመዝገብ ለሌሎች የማይዳሰሱ ቅርሶች ህልውና አስተዋጽኦ የሚያበረክት፣ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር የባህል ትስስርን የሚያጠናክር፣ የአገሪቱን መልካም ገጽታ የሚገነባና የቱሪዝም ልማቱን የሚያጎለብት እንደሆነም አክለዋል አቶ ገዛኸኝ።

የቅርሱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ወጣቶች የስርዓቱን ታሪካዊ አመጣጥና ጠቀሜታ ከአባቶች መከታተልና መተግበር እንዲሁም ስርዓቱ የሚከናወንባቸውን ስፍራዎች ተንከባክቦና ጠብቆ ማቆየት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የገዳ ስርዓትና ሌሎችም ቅርሶች በስርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካተው ለትውልድ የሚተላለፉበት ሁኔታ ቢመቻች ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ዋጋሪ በበኩላቸው ስርዓቱ የዘመናዊው ዴሞክራሲ መሰረት ከሆኑ እሴቶቹ በተጨማሪ አገሪቱ ከፈረመቻቸው ስምምነቶች ጋር ተስማሚ ነው ይላሉ።

እነዚህ ሁኔታዎች በዩኔስኮ መመዝገብ የሚያስችለውን አቅም ፈጥሮለታል በሚለው ሃሳብም ይስማማሉ።

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ‘የኢሬቻን ስርዓት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ ነው’ የሚል ግንዛቤ መኖሩን ገልጸው ኢሬቻ ከገዳ ስርዓት መገለጫዎች አንዱና በስርዓት ውስጥ የሚካተት መሆኑን መረዳት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የማኅበረሰቡ እሴቶች ሳይሸራረፉና ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን በመግለጽ።

ከገዳ ስርዓት ባለፈ ሌሎች የሚዳሰሱ ቅርሶችን ለማስመዝገብ ጥናቶች እየተካሄዱ እንደሆነም ተናግረዋል።

ቢሮው የገዳ ስርዓቱን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል – (ኢዜአ ) 