ኤጀንሲው ለህብረተሰቡ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣን አገልግሎት እየሰጠ ነው

የፌደራል የሰነዶች ማረጋጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የቴክኖሎጂ የቴክኖሎጂ ዓቅሞችን ተጠቅሞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታወቀ ፡፡

 

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ እንዳመለከቱት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የተለያዩ ፈጣን መረጃ አገልግሎት የሚሰጡባቸው ዘዴዎች  ዘርግተዋል  ፡፡

 

ከነዚሁም አንዱ በ888 ነጻ የስልክ መስመር መረጃ ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም በድህረ ገጽ በwww.w.daro gov.et ዝርዝር መረጃ አሰጣጥ መስፈርቶችን ማግኘት እንደሚችሉም አመልክተዋል ፡፡

 

የአገልግሎት ዓይነቶችም የኑዛዜ የስጦታ ውሎች ልዩ ልዩ ሰነድ የማረጋገጥ ስራዎችን ለሚፈልጉ በህግ አግባብ አረጋግጦ የመስጠት ስራ መሆኑን ጠቅሰዋል  ፡፡

 

በተለይ ውክልናና ሺያጭን በተመለከተ በድህረ ገጻቸውን ላይ በመግባት የቀጥታ አገልግሎት ስላለ ያንንን መረጃ መልተው ወደ ኤጀንሲው ሲመጡ የአገልግሎት ክፍያ ብቻ በመፈጸም መጠቀም እንደሚችሉ አስታውቀዋል ፡፡

 

ይህም ባለጉዳዮቹ ውል ለማጻፍ የሚያወጡት ወጪ ሳይኖር መገልግል የሚችሉበት ስርዓት የዘረጉ መሆናቸውን ነው ያስረዱት ፡፡

 

ይሁንና ኤጀንሲው ፈጣን የቴክኖሎጂ አገልግሎት ቢዘረጋም ህብረተሰቡ በስፋት እየተገለገለበት አይደለም ነው ያሉት ፡፡

 

ኤጀንሲው ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ለማሳደግ እንዲችል በአገልግሎት አሰጣጥ የሚታዩትን ክፍተቶች እስከበላይ ኃላፊ በግልጽ መንገር ይችላሉ ብለዋል ፡፡

ዓምና በቀን እስከ 4ሺ 900 ተገልጋዮችን ሲያስተናግድ የቆየ ተቋም ነው ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ፡አሁን ቁጥሩ በቀን እስከ 5ሺ 500 ተገልጋዮች ከፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን አስታውቀዋል ፡፡

 

ዘንድሮ ኤጀንሲው ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ተገልጋዮችንና ጉዳዮችን በማሰተናገድ 350 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ይታወቃል ፡፡