ሚኒስቴሩ ከዩኤስ አይድ ለጤና አግልግሎት የሚውል 30ሚሊየን ዶላር ማግኘቱን አስታወቀ

ዩ ኤስ አይድ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ አራት ክልሎች ለጤና አገልግሎት የሚውል ድጋፍ ማድረጉን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከዩ ኤስ አይድ ጋር በመተባበር ልዩ ድጋፍ የሚሹ በኢትዮጵያ ሶማሌ፣ደቡብ ለሚገኘው ቤንቺማጂ ዞን ፣ጋምቤላ እና ዓፋር ክልሎች ለሚገኙ 56 ጤና ጣብያዎች ላይ በ2017  የፈረንጆች ዓመት ለእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት የሚውል መሆኑን የሚኒስቴሩ የእናቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ ስንታዮህ አበበ አስታውቀዋል ፡፡

ድጋፉ በጤና ተቋሞቹ ለሚመጡ እናቶች የቅድመ ወሊድ፣ የወሊድና የድህረወሊድ አገልግሎት በነፃ እንዲያገኙ ለማድረግ ታስቦ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ100 ሺ ወላድ እናቶች 11 ሺዎቹ ሕይወታቸውን ያጣሉ ፡፡

ይህ ችግር የሚበረታው ደግም ልዩ ድጋፍ በሚሹ አራቱም ክልሎች  በጤና ተቋም የመገልገል ልምዳቸው አናሳ በመሆኑ ነው ያሉት ፡፡ 

በአሁኑ ወቅት በጤና ተቋም የሚገለግሉ እናቶች 73 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

ድጋፉ ይህንን ለማጎልበት ታስቦ የተሰጠ መሆኑን አስተባባሪው  አመልክተዋል ፡፡

እናቶች በእርግዝና ወቅት በጤና ተቃማት ቅድመወሊድ፣  በወሊድና በድህረወሊድ ክትትል  እንዲያደርጉ ፤ ከጤና ተቋማት ርቀት ቦታ ላይ የሚኖሩ እናቶችም ዘጠነኛ ወራቸው ሲሞላ ባካባቢያቸው በተዘጋጀ የማቆያ ጣብያ ላይ በመቆየት የወሊድ  አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑ ጠቁመዋል፡፡

እናቶች ለራሳቸውና ለህጻናቱ ደህንነት ሲሉ በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ሊጠቀሙ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት ፡፡

የጤና ባለሙያዎች ርህራሄና አክብሮት በተሞላበት ሙያዊ አገልግሎት እንዲሰጡዋቸው አቶ ስንታዮህ አሳስበዋል ፡፡