በቀድሞው የኦሮሚያ የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሃላፊ በነበሩት አቶ ዘላለም ጀማነህ ላይ የቀረበባቸውን የሙስና ወንጀል ክስ ለመስማት ተይዞ የነበረውን ቀጠሮ መራዘሙን በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ ፡፡
የክልሉ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቶ ዘላለም እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ 12 ግለሰቦች ላይ 14 ክሶችን መመስረቱን ጠቅሷል ፡፡
ክስ ከተመሰረተባቸው ግለሰቦች መካከል አቶ ዘላለምን ጨምሮ 6ቱ ብቻ በመገኘታቸው ሁሉም ተከሳሾች ቀርበው ክሱ እንዲነበብ ነበር ችሎቱ ቀጠሮ ይዞ እንደነበረ ነው የተመለከተው ፡፡
ይህን እንጂ ፖሊስ ሌሎች 6ቱ ያልቀረቡ ተከሳሾች በችሎቱ ተሟልተው ክሱን ለማንበብ እና ሌሎች አቤቱታዎችን ለመቀበል ለህዳር 12/2009 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ገልጿል ፡፡
አቶ ዘላለም ጀማነህ በ14 ከባድ የሙስና ወንጀሎች ክስ ቀርቦባቸዋል ነው ያለው ፡፡
ከክሶቹ ውስጥ የመንግስት እና የህዝብ ንብረቶችን በስማቸው በማዞር፣ በህግ ወጥ መንገድ ያገኙትን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ መያዝ እና ከገቢ በላይ ሀብት ማፍራት የመሳሰሉትን ነው የጠቀሰው -(ኢብኮ)፡፡