የኢፌዲሪ የመድሐኒት ፈንድ አቅርቦት ኤጀንሲ በ18 ነጥብ 8 ቢልየን ብር መድሐኒት፣ የህክምና መሳሪያዎችና መገልገያዎች ለጤና ተቋሞች ማዳረሱን አስታወቀ ፡፡
ባሳለፍነው በጀት ዓምት ለመላው የሀገሪቱ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣብያዎችና ጤና ኬላዎች ተይዞ የነበረው በጀት 15 ነጥብ 3 ቢልየን ብር ቢሆንም የህክምና መሳሪያዎች ዋጋ ከፍ በማለቱ በ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ለመጨመር መገደዳቸውን የኤጀንሲው የህዝብ ግኑኝት ሃላፊ ወይዘሮ አድና በሬ ገልጸዋል ፡፡
ለእናቶችና ህፃናት ወይም ለወሊድ አገልግሎት የሚውለው ይኽው ድጋፍ ከጤና ኬላ እስከ ጀነራል ሆስፒታል በነፃ እንዲያገኙ ይደረግ እና ወጪውን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደሚያካክስ አብራርተዋል፡፡
ጤና ተቋማት የሚያስፈልጋቸውን ቁሳቁስ አስቀድመው ሲያቀርቡ ለጥናቱ ጊዜ የሚሰጥ ከመሆኑም ባሻገር ከግል መድሐኒት ቤቶች ከመግዛት እንደሚያድናቸውም አስረድተዋል ፡፡
የኤጀንሲው 17 ቅርንጫፎች በየዓመቱ የሚጠየቁ የህክምና መሳርያ አገልግሎቶችና መድሐኒት እያከፋፈለ መሆኑን ነው ያስታወቁት ፡፡