ኤች አይ ቪ ኤድስ የሀገሪቱ ከፍተኛ አደጋ መሆኑን በመገነዘብ በተለይም አምራች ኃይሉ ሊጠነቀቅ እንደሚገባ የአዲስ አበባ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣሪያ ጽሕፈትቤት አስገነዘበ ፡፡
በበሽታው የሀገሪቱ አምራች ሃይል የሆኑት ሴተኛ አዳሪዎች ፣ወጣቶችና እስረኞች ዋንኛ ተጠቂ መሆናቸውን የጽሕፈትቤቱ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ፕሮግራም አስተባባሪ ወይዘሮ ፈለቀች አንዳርጌ ገልጸዋል፡፡
በሽታው በከቶሞች የመቀነስ ሁኔታ ቢኖርም እንደ አገር ግን ከፍተኛ አደጋ ሆኖ መቀጠሉን ነው ያስረዱት ፡፡
ይህም በህብረተሰቡ በበሽታው አደጋ ላይ መዘናጋት እንደሚታይ እና ለዚሁም በየጊዜው አጀንዳ በማድረግ ሊጠነቀቅ ይገባል ነው ያሉት ፡፡
በነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ከወትሮው በበለጠ ከፍተኛ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሊከናወን እንደሚገባ ነው ያስረዱት ፡ ፡
ወጣቱና ማህበረሰቡ የበሽታው መነሻ ፣የሚያስከትለው አደጋና ራሳቸውን ለመከላከል በሚችልበት ሁኔታ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ነው ያመለከቱት ፡፡
ለዚሁም በሽታውን ለመከላከል የሚያስች አዲስ መመሪያ መውጣቱን አስታውቀዋል ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ መስሪያቤቶች ከዓመታዊ ባጀታቸው በሽታውን ለመከላከል አንድ በመቶ በጀት መያዛቸውን አሰታውቀዋል ፡፡
በሀገሪቱ የበሽታው ስርጭት መጠን 1ነጥብ 2 በመቶ መሆኑንና በየዓመቱ 2ሺ ወገኖች በበሽታው እየተያዙ መሆናቸው ተመልክቷል ፡፡
በሀገራችን በሽታው እ አ ኤ በ2030 ለመግታት ግብ የተቀመጠ ሲሆን ፤22ኛው የኤች አይ ቪ ኤድስ በዓል በየክልሉ በተለያዩ ዝግጅቶች ዛሬ እየተከበረ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል ፡፡
ትርጉም በሪሁ ሽፈራው