በአዲስ አበባ ከተማ የአሊያንስ ትራንስፖርት 100 አውቶቡሶች ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ ።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ አማረ አውቶቡሶቹ ከመጭው ሰኞ አንስቶ አገልግሎት የሚሰጡባቸው መስመሮች ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍላጎት አለባቸው ተብለው የተመረጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አውቶቡሶቹ በመዲናዋ በተመረጡ 13 መስመሮች አገልግሎት እንደሚሰጡ ነው የገለጹት ።
ፒያሳ፣ አውቶቡስ ተራ፣ መገናኛ፣ ሜክሲኮና አራት ኪሎ የአውቶቡሶቹ መነሻ ስፍራዎች ናቸው።
ከአራት እስከ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚጓዙት አውቶቡሶቹ ከ1 ብር ከ50 ሣንቲም እስከ 12 ብር ታሪፍ ወጥቶላቸዋል።
ባለስልጣኑ መንግስት ከቀረጥ ነጻ ያስገባቸውን የማህበሩን 100 አውቶቡሶች አገልግሎት መጀመር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል ።
አውቶቡሶቹ የታሪፍ ማቆራረጥና ከታሪፍ በላይ ክፍያ የሚጠየቅባቸው ተብለው በተለዩ አካባቢዎች እንደሚሰማሩም አስታውቀዋል ።
ለመዲናዋ አጎራባች ከተሞች አገልግሎት እንደሚሰጡም ጠቁመዋል።
የአውቶቡሶቹ አገልግሎት መጀመር የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ፍላጎት በማሟላት ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር አማራጭም ይፈጥርለታል ብለዋል አቶ ምትኩ።
በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ተጨማሪ 200 የአሊያንስ አውቶቡሶች ወደ አገር ውስጥ እንደሚገቡ ጠቁመው ህብረተሰቡ በህዝብ ትራንስፖርት የመጠቀም ባህሉን እንዲያዳብር አሳስበዋል።
የአሊያንስ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ በ25 አውቶቡሶቹ በ11 የተመረጡ ቦታዎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል- (ኢዜ