ኢትዮጵያውያን በዓለ ጥምቀቱን ጠብቀው ለዓለም ሊያስተዋውቁት እንደሚገባ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አስገነዘቡ ፡፡
በዓለ ጥምቀቱን የህዝቦቻችን አንድነት መጠበቂያ ጠንካራ ዘዴ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን ጠብቀው ለዓለም ሊያስተዋውቁት እንደሚገባ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አባ ማትያስ አስገንዝበዋል ፡፡
በጃንሜዳ በተከበረው በዓለ ጥምቀቱ የተገኙት አባ ማትያስ ባስተላፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦችን በአንድነት አስተሳስሮ የሚያቀራርብ ጠንካራ ኃይል መሆኑን ገልጸዋል።
የከተራና የጥምቀት በዓላት የክርስትና እምነት ተከታዮች፣የውጭ ጎብኚዎች፣ ካህናት፣ ዲያቆኖትና መዘምራን በድምቀትና ፍጹም ሰላማዊ በመሆነ መንገድ አክብረው ውለዋ