ዶ/ር ቴድሮስ ከአምስቱ የዓለም ጤና ድርጅት ዕጩዎች ውስጥ ተካተቱ

የዓለም ጤና ድርጅት  ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ባካሄደው ምርጫ ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም ድርጅቱን ለመምራት ከሚፎካከሩት አምስት ዕጩዎች ውስጥ ሆኑ ።

የስራ አስፈፃሚ  ቦርድ አባላቱ  ለድርጅቱ  ዋና ዳይሬክተርነት በአባል አገራት ከቀረቡ እጩዎች  ውስጥ የመጀመሪያ ማጣሪያ ምርጫቸውን  አካሂደዋል ።

ቦርዱ  ከቀረቡት ስድስት ዕጩዎች አምስቱን ለመለየት ባካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ስነ  ስ ርዓት ኢትዮጵያንና አፍሪካን ወክለው የቀረቡት ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም አምስቱ ውስጥ ተካተው ተመርጠዋል።

ከዶክተር ቴድሮስ በተጨማሪ  ለውድድር የቀረቡት አምስት ዕጩዎች ዶክተር ፍላቪያ  ቡስትርዮ፣ፕሮፌሰር ፍሊፕ ዱስቴ ፍላዚ ፣ዶክተር ዴቪድ ናባሮና ዶክተር ሳኒያ ኒሽታር    የተባሉ መሆናቸው ነው የተመለከተው

የቦርዱ ስራ አስፈፃሚ አባላት አምስቱን ተፎካካሪዎች ቃለ መጠይቅ በማድረግ ሶስት የመጨረሻ ተፎካካሪ ዕጩዎችን ዛሬ ይፋ ያደርጋሉ ተብሉ  ይጠበቃል።

ሶስቱ የመጨረሻ ዕጩዎችም አባል አገራቱ የፊታችን ግንቦት በሚያካሄዱት ጠቅላላ ጉባኤ በቀጥታ የድርጅቱ  ዋና ዳይሬክተር የሚሆነውን አሸናፊ የሚለይ ይሆናል።

ተመራጩ  ዋና ዳይሬክተር ደግሞ እ ኤ አ ከሐምሌ 1/2017 ጀምሮ መደበኛ  ስራውን ይጀምራል-(ኢብኮ) ።