በዓፋር ክልል የሚገኘው እሳተጎሞራ የቀለጠ ድንጋይ ጎርፍ መቆሙን የክልሉ አደጋ መከላከል ጽሕፈት ቤት አስታወቀ ፡፡
ዓለም አቀፍ ቱሪስት መስህብ የእሳተ ጎመራ ጉድጓድ ከነበረው ተመሳሳይ የሆነ ሌላ ግዙፍ ጉድጓድ መፍጠሩን ገልጸዋል ፡፡
የእሳተ ጎመራው አጠቃላይ ሁኔታ ለማወቅ ነገ ወደ አከባቢው አንድ አጥኚ ቡድን ለመላክ መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል፡፡
የዓለምና የአገር ውስጥ ቱሪስቶች መስህብ የሆነው አስደናቂው ኤርታዓሌ እሳተ ጎመራ ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ ፍሳሹ ገንፍሎ መልቶና ከዋናው መያዣው ጉድጓድ ወጥቶ በብዛት እየፈሰሰ መሆኑን በአራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኮሌጅ በምድር ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህር ፕሮፌሰር ገዛኸኝ ይርጉ መግለጻቸው ይታወቃል ፡፡
እሳተጎሞራው በአሁን ሰዓት የሚያመጣው ችግር ባይኖርም እየቀጠለ ከሄደ ግን አደጋ ሊያመጣ እንደሚችልም ማስጠንቀቃቸውንም እንዲሁ ፡፡
አሁንም ወደ ስፍራው መሄድና ለወደፊቱ ለጥናት እንዲያመችም መታየት መመርመር እንዳለበት ነው የተመለከተው ፡፡