የመጀመሪያው የሹፌሮች ቀን ተከበረ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የሹፌሮች ማሕበር የመጀመሪያውን የሹፌሮች ቀን በዓል በድምቀት አከበረ፡፡

በዓሉ “ክብር ለሹፌሮቻችን” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢንጂነር ሰለሞን ኪዳኔ በበዓሉ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የትራፊክ አደጋ በገዳይነቱ ከኤችአይቪ/ኤድስና የወባ በሽታ ሁሉ የከፋ በመሆኑ ችግሩን ለማቃለል መንግስት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶታል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የትራፊክ አደጋን መጠን መቀነስ እንደተቻለ ዶክተር ኢንጂነር ሰለሞን አክለው ገልጸዋል፡፡

የበዓሉ መከበር በተለይም ከትራፊክ አደጋ የፀዳ የትራፊክ እንቅስቃሴ ለማስፈን፣ በሀገሪቱ ዕድገት ላይ ሹፌሮች እያበረከቱት ላሉት አስተዋፅኦ ምስጋናና እውቅና በመስጠት ክብራቸውን ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ታውቋል፡፡

በትራፊክ አደጋ ሹፌሮች 85 በመቶ ያህል ሕይወታቸው ለአደጋ ተጋላጭ እነደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በዕለቱ ለምስጉን ሞዴል ሹፌሮች የእውቅናና የምስጋና ሰርትፊኬት በመርከቱን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡