በቶታል ስፖንሰር አድራጊነት የሚካሄደው የ2017 የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ዛሬ ካምፓላ እና በቻር ላይ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀምራል፡፡
የዩጋንዳው ቻምፒዮን ኬሲሲኤ በሜዳው የአንጎላውን ፕሪሜሮ ደ አጎስቶን ሲያስተናግድ ለውድድሩ እንግዳ የሆነው የአልጄሪያው ጄኤስ ሳዎራ የናይጄሪያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊውን ኢንጉ ሬንጀርስን ይገጥማል፡፡
የኢትዮጵያው ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዳሜ ከሲሸልሱ ኮት ዲ ኦር ጋር በፕራስሊን ይጫወታል፡፡
የፊሊፕ ኦሞንዲ ስታዲየም ለጨዋታው ቡቁ ነው በመባሉ የኪሲሲኤን እና ፕሪሜሮ አጎስቶን ጨዋታ ያስተናግዳል፡፡
የስታዲም የተመልካች የመያዝ አቅም 10ሺ ቢሆንም 5ሺ 600 ተምልካቾች ብቻ ወደ ስታዲየም እንዲገቡ ይፈቀድሏቸዋል ብሏል የዩጋንዳው ክለብ፡፡
ኢንጊ ሬንጀርስ ወደ ሰሜን አፍሪካ አቅንቶ ጄኤስ ሳዎራን ይገጥማል፡፡
ዛሬ 16፡00 – ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶሪቲ (ዩጋንዳ) ከ ሲዲ ፕሪሜሮ ደ አጉስቶ (አንጎላ) (ፍሊፕ ኦሞንዲ ስታዲየም)
19፡00 – ዩነስ ስፖርቲቭ ደ ላ ሳዎራ (አልጄሪያ) ከ ኢንጉ ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ) (ስታደ ኦገስት 20 1955) ዘገባው የሶከር ኢትዮጵያ ነው ፡፡