ፌደሬሽኑ በሥራ አፈጻጻምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን ምክር ቤት ያለፉትን ሦስት ዓመታት  የሥራ አፈጻጻም ሪፖርትን በመገምገም  የቀጣይ አምስት ዓመታት ስትራቴጂክ  አቅጣጫዎች ላይ  ውይይት አደረገ።         

ባለፉት ሦስት ዓመታት ፌደሬሽኑ የሴቶችን የትምህርት ተደራሽነት ለማሳደግ   የተለያዩ  ድጋፎችን  ሲያደርግ ከመቆየቱም በላይ  የሴቶችን  መብት በማስጠበቅና ጎጂ  ልማዳዊ ድርጊቶችን  በመከላከል ረገድ እንቅስቃሴ መደረጉን  የፌደሬሽኑ ፕሬዚደንት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ገልጸዋል።         

ፌዴሬሽኑ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት  የሴቶችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ  ለማሳደግ ትኩረት ሠጥቶ እንደሚሰራ የጠቆሙት ወ/ሮ አዜብ ሁሉም  የፌዴሬሽኑ አባላት  በተመረጡባቸው አካባቢዎች  ይህንን እውን ለማድረግ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ።       

 ሁሉም የክልል አመራሮች  ለሴቶች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ  ትብብራቸው  የላቀ እንደሚሆን እምነታቸውን የገለጹት ወ/ሮ አዜብ  የፌዴሬሽኑን የገንዘብ ምንጭ በማጠናከር ለፌደሬሽኑ ግቦች ስኬት መታገል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ  ሴቶች ፌደሬሽን  ምክር ቤት    በመላ አገሪቱ  ከ 8 ሚሊዮን  በላይ  አባላት እንዳሉት ይታወቃል።

 ( ትርጉም  :በሰለሞን ተስፋዬ)