የሞጆ -ሐዋሳ የፈጣን መንገድ 12 በመቶ ተጠናቀቀ

የሞጆ-ሓዋሳ የፈጣን መንገድ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 12 በመቶ  መጠናቀቁን  የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ ።

የቻይና ሬል ዋይ ሰቨንዝ ግሩፕ የሞጆ -አዋሳ የፈጣን መንገድ ፕሮጀክትን በ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ለማከናወን  ከሁለት ዓመት በፊት   መስማማቱ ይታወሳል ።   

የመንገድ ፕሮጀክቱን  ወጪ  የሚሸፈነውም ከኢትዮጵያ መንግሥት  በተመደበ በጀትና   ከአፍሪካ ልማት ባንክ  በተገኘ ብድር ነው ።  

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለዋልታ እንደገለጹት የሞጆ -መቂ የፈጣን መንገድ ፕሮጀክትም የሞጆ -ሐዋሳ የፈጣን መንገድ  አካል መሆኑንና የሞጆ -ሃዋሳ ፈጣን መንገድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ  በ2011 ዓም  ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል ።

እስካሁን ድረስ የሞጆ-ሐዋሳ ፈጣን መንገድ የግንባታ ሥራ  በጥሩ  ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ሳምሶን  የመንገድ ግንባታ ሥራ  አፈጻጻም ፕሮጀክቱ  በተያዘለት የጊዜ  ሰሌዳ እንደሚጠናቀቅ ያመላክታል ብለዋል ።

የመንገድ ፕሮጀክቱን   የጥራት ደረጃውን  ለመጠበቅም  ልምድ ያላቸው  አማካሪዎችና ተቆጣጣሪዎች   ክትትል እያደረጉ መሆኑን አቶ ሳምሶን አስረድተዋል ።

የፈጣን መንገድ ፕሮጀክቱ  የተቀሩት ሦስር ምዕራፎች  መቂ-ዝዋይ ፣ዝዋይ-አርሲ ነገሌና አርሲ ነጌሌ-ሃዋሳ የመንገድ ግንባታዎች  መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ሳምሶን   በአጠቃላይ 145 ኪሎሜትር የሚረዝመው መንገድ ከአገር ውስጥና ከውጭ  በተገኘ  ገንዘብ ይገነባሉ ብለዋል ።          

የዓለም ባንክና የቻይና ኤግዚም  ባንክ  የፈጣን  መንገዱ  በገንዘብ  በመደገፍ በኩል  ዋነኛ  የገንዘብ ተቋማት  ናቸው  ።

( ትርጉም : በሰለሞን ተስፋዬ)