አስተዳደሩ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ በደረሰው አደጋ የሰው ሕይወትና ንብረት በመጥፋቱ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገለጸ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ  በተለምዶ ቆሼ በተባለው አካባቢ አደጋው የደረሰው ትናንት ከምሽቱ 2:00 ገደማ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ፤ አስተዳደሩ በተከሰተው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች የተሰማውን ልባዊ ሐዘን በራሱና በከተማዋ ነዋሪዎች ስም ገልጿል።