የኢትዮጵያ ላንድ ኦፍ ኦሪጅን በሚል የተዋወቀው የኢትዮጵያ የቱሪዝም መለያ የአማርኛ ትርጉሙ ˝ምድረ ቀደምት˝ በሚል ተተርጉሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ይፋ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው ፡፡
በጉባኤው ላይ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ በየጊዜው የሚነሱ ተመሳሳይ ችግሮችን ለመፍታት አሁንም ከፍተኛ ትኩረትና የቅንጅት ስራ እንደሚያስፈልግ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም አስታውቀዋል፡፡
በጉባኤው እየተደረገ ባለው ውይይት ዘርፉን ለማዘመን ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም አንጻር አሁንም ሰፊ ስራዎች እንደሚቀሩ ተመልክቷል፡፡
ከፓርኮች ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ የሚነሱት ችግሮች እየተፈቱ አለመሆኑ እና ከቅርሶች እድሳት ጋር በተያያዘ ደግሞ የነባር ይዞታዎች መጥፋት ችግሮች መኖራቸው እንዲሁም በዘርፉ አሉ ተባሉ ሌሎች ችግሮች በምክር ቤቱ አባላት ተነስተዋል።
ለጥያቄዎቹም የምክር ቤቱ የቦርድ ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ምላሽና አቅጣጫዎች ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል-(ኤፍ ቢ ሲ) ፡፡