ቢሮው ውጤት ተኮር አሠራረን የሚያጎለብት ሥልጠና መሥጠት ጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት  ቢሮ ውጤት  ተኮር አሠራሮችን  የሚያጎለብት የአሠልጣኞች ሥልጠና መሥጠት መጀመሩን  አስታወቀ ።

የቢሮው የሥልጠናና ጥናት ዳይሬክተር ወይዘሮ ዘበናይ ሸጋና ለዋሚኮ እንደገለጹት ቢሮው 600 ለሚሆኑ የሲቪል ሰርቪስ አመራሮች  ለአራት ቀን የሚቆይ የአሠልጣኞች ሥልጠና መሥጠት ተጀምሯል ።

እንደ ወይዘሮ ዘበናይ ሥልጠናው በአራት  ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩርና ከ88 ተቋማት ለተውጣጡ አመራሮች  በሁለት  ቦታ  የተከፋፈለ ሥለጠና  እየተሠጠ ይገኛል ።

የሥልጠናው ተሳታፊዎች በተለያዩ ተቋማት የክፍል  ኃላፊዎችና  ምክትል  ኃላፊዎች መሆናቸውን የሚናገሩት አቶ ዘበናይ  በቀጣይ   ኃላፊዎቹ  በሥልጠናው ያገኙትን  ተሞክሮ  በሥራቸው ለሚገኙት  ሠራተኞች  ያካፍላሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል ።

ሥልጠናው በዋናነት በሥራ ጊዜ አጠቃቀም ፣ኃላፊነትን በመወጣት ፣ በካስኬዲንግ ተግባራዊነትና በሥራ አፈጻጻም ግምገማ ርዕሳነ ጉዳዮች ላይ  የሚያተኩር መሆኑን  አቶ ዘበናይ አብራርተዋል ።  

እየተሠጠ የሚገኘው ሥልጠና  ዓላማ  የሲቪል ሰርቪስ  ሠራተኛው የሥራ  ጊዜውን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲያውል ፣ የተገልጋይ እርካታን እንዲያሳድግና የክህሎትና እውቀት  ክፍተቱን ለመሙላት እንዲችል መሆኑን  አቶ ዘበናይ አስረድተዋል ።

በአዲስ አበባ ከተማ  የሲቪል ሰርቪስ አሠልጣኞች  ሥልጠና  በሚቀጥለው ወር ይጠናቀቃል ተብሎ የሚገመት ሲሆን በአጠቃላይ   3ሺ አመራሮችን ለማሳተፍ ታቅዷል ።