ዋልታ ቴሌቪዥን መደበኛ ፕሮግራሙ መጀመሩን ኮርፖሬቱ አስታወቀ

ዋልታ ቴሌቪዥን ዕለታዊ ዜናና ልዩ ልዩ መደበኛ ፕሮግራሞቹን ይዞ ዛሬ መጀመሩን የዋልታ ሚድያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት አስታወቀ ፡፡

የኮርፖሬቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተተካ በቀለ እንዳስታወቁት ፤ተመልካቾች ሃገሬ እና ኢትዮጵያ ዛሬ በተሰኙት ዘጋቢ ፊልሞቹ የሚያውቁት ዋልታ፣የቴሌብዥን ስርጭት መጀመሩን አብስረዋል ፡፡

በዚህ ሁኔታ የተጀመረው ዋልታ በመጀመሪያው የታሪክ ምዕራፉ ከ1986 ዓም እስከ 1998 ዓም ባሉት ዓመታት ዕለታዊ ዜናዎችን፣ለሬድዮ ፕሮግራም የሚሆኑ ቃለ መጠይቆችን፣ሃተታ ጽሁፎችን አዘጋጅቶ፣በወቅቱ ለነበሩት የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ የመገናኛ ብዙሃን መረጃን መመገቡን ጠቅሰዋል፡፡

የኤርታዓሌ ዝቅተኛ ቦታዎችን ጨምሮ በርካታ ዘጋቢ ፊልሞች የተሰሩት በዚህ ምዕራፍ እንደነበረም እንዲሁ ፡፡

ዋልታ ዛሬ ከደረሰበት ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ልዩ ልዩ የታሪክ ምእራፎችን መግለጡን ነው የገለጹት ፡፡

ጥንስሱ ከለውጥ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ዋልታ በወቅቱ የነበረውን ውዥንብርና የመረጃ ክፍተት ለመሙላት በታህሳስ ወር በ1986 መቋቋሙን አንስተዋል ፡፡

ዋልታ በሀገሪቱ የነበረው የመረጃ ክፍተት ለመሙላት የተቋቋቋመ እንደነበረም ጠቁመዋል ፡፡

ይህም የደርግ ስርዓት ማክትምን ተከትሎ የተቋቋሙት የህትመት ሚዲያዎች የዓቅም ውስንነት ያለባቸው እንደነበሩ የጠቆሙት አቶ ተተካ ፤አንዳንዶቹም ስርዓቱን ሲያገለግሉ የነበሩ በመሆናቸው ፈጣን ፣ ሚዛናዊና ተዓማኒ መረጃ የመስጠት ክፍተት እንደነበረባቸው ነው ያብራሩት ፡፡

በመጀመሪያው ምዕራፍ መጨረሻ ግን ዋልታን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተ ሆኖ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ተተካ ከዜና ሽያጭ ብቻ በሚያገኘው ገቢ ለሰራኞቹ ደሞዝ መክፈል እንኳን ተቸገሮ እንደነበር ነው የጠቆሙት፡፡

ይህን ዘመን ተከትሎ በተቋሙ የታሪክ ምዕራፍ ሆኖ የተመዘገበው ከ1998ዓም እስከ 2006 ዓም የማሽቆልቆል ታሪክ የቀለበሰ እንደሆነም አስታውቀዋል ፡

እንደ ዋና ስራ አሰፈጻሚው ገለጻ፤አዳዲስ ስራዎችን ይዞ የመጣው ምዕራፉ የተቋሙ እድገት ጉዞ ሆኖ ተመዝግቧል ፡

በዚህ በእመርታ ጊዜ ዋልታ እየሰራቸው የሚገኙት ስራዎችየማህበራዊን  ፣የሚዲያና  የገበያ ጥናትን ይጨምራል ነው ያሉት ፡፡

የሀገሪቱን የቢል ቦርድ ማስታወቂ ያዘምናል የተባው የዲጂታል ሳይን ኤጅ ስራም በሰፊ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ለሚዲያዎች ይዘት የሚያቀርብ የይዘት ማዕከልም ይቋቋማል ነው ያሉት ፡፡

በዋልታ ሚድያና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት የሚዲያ መሳሪያዎች ጥገና፣የፊልምና የጋዜጠኝት ሙያ ስልጠናም በሚቀጥሉት አምስት አመታት የሚተገበሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል ፡፡

አርታኢ -በሪሁ ሽፈራው