ከሰበታ በሬ ገዝተው ወደ አዲስ አበባ ሲያመሩ የነበረ ግለሰብ በገዙት በሬ ተወግተው ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ ።
የሰበታ ከተማ ፖሊሲ ጣቢያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር አደም ሐሰን በአደጋው ህይታቸውን ያጡት ግለሰብ አቶ ተጎዱ ጌታቸው ነዋሪነታቻው በላፍቶ ክፍለ ከተማ በበኣሉ ዋዜማ ወደ ሰበታ ሄደው የገዙትን በሬ በክፍት ተሽከርካሪ ጭነው ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ነው ።
እንደ ኮማንደሩ ገለጻ ፤አሳዛኙ አደጋ የተከሰተውም በአይሱዙ የተጫነው በሬ ከግብይት ስፍራው ተነስቶ ትንሽ ከተጓዘ በኋላ ሰበታ ከተማ 03 ቀበሌ ሲደርስ ከተሽከርካሪው ላይ ዘሎ ይወርዳል።
በሬውን የገዙት ግለሰብም የበሬውን መውረድ ሲያዩ ከተሽከርካሪው በመውረድ በሬውንን ለመያዝ ከኋላው ይከተሉታል።
በዚህ አባሮሽ ላይ እያሉ በሬው ወደ ኋላ በመመለስ ካሳደዳቸው በኋላ አንገታቸው ሰር ይወጋቸዋል።
በውጊያው ክፉኛ የተጎዱት ግለሰብ ለህክምና ወደ አለርት ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸው ሊተርፍ አልቻለም -(ኤፍ.ቢ.ሲ) ።