በአቃቂ ክፍለ ከተማ በገበያ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 750ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

 

በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ቄራ በሚገኝ በገበያ ማእከል ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል።

በገበያ ማእከሉ ላይ ዛሬ ከጥዋቱ 1 ሰዓት ከ10 ላይ በደረሰው የእሳት አደጋም 750 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን አስታውቋል።

ባልስልጣኑ የተነሳዉ አደጋ አሁን ላይ በቁጥጥር ስር መዋል ችሏል ብሏል ።

አደጋውን ለመቆጣጠር ባለስልጣኑ ባደረገው ጥረትም ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማዳኑን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ አስታውቋል።

በአደጋው በሰዉ ህይወት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም ሲሉ አረጋግጠዋል -(ኤፍ.ቢ.ሲ) ።