ደቡብ ኮሪያ በአዲስ አበባ የማህበረስብ አቀፍ ማዕከል ለመክፈት ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት መፈፀሟን የሀገሪቷ መከላከያ ሚንስትር ገለጸ፡፡
የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚንስትር ዴኤታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታውና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት ስምምነቱ ትላንት እንደተፈረመ ገልጿል፡፡
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1950 አስከ 1953 በነበረው የሁለቱ ኮሪያውያን ጥርነት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በብቸኝነት ወደ ደቡብ ኮሪያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን በመላክ ላበረከተችው አስተዋጽኦ ድጋፍ ለሚሆነው ፕሮጄክት አካል እንደሆነ ታውቋል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ለዘማች ቤተሰቦች መሰረታዊ ፍላጎቶች አገልግሎት የሚሰጠው ማዕከል በነሐሴ 2010 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር ተጠቁሟል፡፡
እንደ ኮሪያው መከላከያ ሚንስቴር መረጃ ኢትዮጵያ 3ሺህ 500 ያህል ወታደሮችን ወደ ደቡብ ኮሪያ ልካ እንደነበርና ከነዚህ መካከል 650 የሚሆኑት በጦርነቱ የሞትና የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተመልክቷል፡፡
በታይላንድና ኮሎምቢያ የተከፈቱ አግልግሎት መስጫ ማዕከላትን ጨምሮ በኮሪያ ከተገነቡት የአዲስ አበባው ሶስተኛው እንደሚሆን ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬትስ ዘግቧል፡፡