በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ልዩ ስሙ ሩፋኤል በሚ ባለው አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የውሀ ችግር መጋለጣቸውን ገልፀዋል፡፡
ይህንኑ ችግራቸውንም ጉዳዩ ለሚመለከተው የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም መፍትሄ አለማግኘታቸውን ነው የተናገሩት፡፡
የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ወርቁ ገኖ ችግሩ እንዳለ በመግለፅ ችግሩ የተከሰተው ለአካባቢው ውሃ ከሚያቀርቡ መስመሮች መካከል በአንዱ ላይ ብልሽት በማጋጠሙና በአካባቢው እየተከናወነ ያለውን የመንገድ ስራ ተከትሎ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡