47 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል

በሞዛምቢክ በእስር ላይ የነበሩ 47 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ትናንት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።  

ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በህገ-ወጥ መንገድ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ድንበር አቋርጠው ሲጓዙ በሞዛምቢክ በእስር ላይ የቆዩ ናቸው።                      

ስደተኞቹ በኢትዮጵያ መንግሥትና በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የጋራ ጥረት ትናንት ምሽት ወደ አገራቸው ገብተዋል።

ቀሪዎቹ ሰባት ስደተኞች ደግሞ ዛሬ ማምሻውን ይገባሉ።

መንግሥት በደቡብ አፍርካ የኢፌዴሪ ኤምባሲ በኩል ባደረገው ጥረት ለአገራቸው በመግባታቸው አመስግነዋል።

ስደተኞቹ የትራንስፖርት ወጪያቸው ተሸፍኖ ወደየመጡበት አካባቢ አንዲመለሱ ተደርጓል።